የተጣራ 500ካሬሜ አሁን ላይ ስንት ነው?


መስከረም 3 2017 ለ11ዱም ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥትር ጽ/ቤት ሴት ባክ ህግ አተገባበርን በሚያትተው ጽሁፍ መሰረት አንዳንድ ባለይዞታዎችና የመሬት ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ጓዶች የሚከተሉትን ነጥቦች ትኩረት ቢሰጧቸው መልካም ነው።

በህጉ መሰረት የሚከተሉትን በዋናነት እንያዝ:-

፩) መሬቱ በሚያዋስነው መንገድ ስፋት መሰረት ግንባታ ለመገንባት የሚቻለው ከወሰኑ ወደ ጊቢው የሚገው (setback) በሜትር 10, 5,3እና2ሜትር ነው።

፪) 15ሜትር እና ከዛ በላይ የሆነ ከሆነ የይዞታው የፊት ለፊት የጎን ስፋት (front width) ከ20ሜ ያላነሰ መሆን ሲኖርበት የቦታው ስፋት set-back ከተቀነሰ በኋላ ከ500ካሬሜ በላይ መሆን እንዳለበት አስቀምጧል።

በዚህ ህግ መሰረት 500ካሬ ሜትር ሆኖ ለግንባታ ብቁ ለመሆን የፊት ለፊቱ ስፋት በትንሹ 20ሜትር መሆን ስላለበት እሱን ይዘን በምሳሌ በቁጥር እናስቀምጥ:-
1)አዋሳኝ መንገዱ 30ሜትርና ከዛ በላይ ከሆነ
*ለሴት ባክ የሚተው ትንሹ 10×20 (200ካሬሜ) ይሆናል
* ተቀናንሶ ለግንባታ ብቁ ለመሆን የቦታው ስፋት በትንሹ 700ካሬሜ ሊሆን ይገባል። የፊት ለፊት ጎን ስፋቱም በትሹ 20ሜ መሆን ይኖርበታል።
* የቦታው ስፋት ከ700ካሬሜ በልጦ የፊት ለፊት ስፋቱ ከ20ሜትር በታች ከሆነ የግንባታ ፈቃድ ለማግኘት ብቁ አይሆንም ማለት ነው።
* ከፊት ለፊቱ በተጨማሪ ግራና ቀኝ መንገዳ ካዋሰነው ለset-back የሚቀናነሰው ስለሚጨምር የቦታው ስፋት ከወጪ ቀሪ 500ካሬሜ ለመሆን በትንሹ የቦታው ስፋት 800ካሬሜ ገደማ ሊሆን ይገባዋል ማለት ነው።

በዚህ መሰረት ለማሳያ ታሳቢ ላደረግነው ታሳቢ 500ካሬሜ በትንሹ 700ካሬሜ በካርታ ያለው ይዞታ መሆን ይኖርበታል ማለት ነው። ከዚህ መስፈርት በፊት 500ካሬሜ ያለው ለሴትባክ ሲቀነስ ቀሪው በትልቁ 300ካሬሜ ይሆናል። ሁለት መቶ ካሬ ያለው ካርታ እንጂ ለግንባታ የሚሆን መሬት የለውም። የይዞታው የጊቢው ርዝማኔ ከ10ሜትር በታች ከሆነም ካርታ እንጂ ለግንባታ ብቁ የሚሆን መሬት የለውም።

በዚህ ስሌትና በወቅቱ ሴትባክ ህግ መሰረት በርካታ ቦታዎች ለግንባታ ብቁ ስለማይሆኑ አዋሳኝ ባለይዞታዎች ይዞታዎቻቸውን በማቀላቀል በጋራ ማልማትን ሊያስቡበት ይገባል።

የሌሎች ቦታዎችንም ይዘት አብሮ በተያያዘው የሴትባክ ህግ መሰረት እየሰሩ መረዳት ይቻላል።

Join The Discussion

Compare listings

Compare